የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች በናይሮቢ እያደረጉት ያለው ውይይት እስከ ነገ ሊቀጥል እንደሚችል የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተለያዩ ሃገሮችና ዓለም አቀፍ ተቋማት፣ ለሰላም ስምምነቱ ተግባራዊነት እንዲሁም ለመልሶ ማቋቋም እና የመልሶ ግምባታ ሥራዎች ድጋፍ እንደሚያደርጉ እየነገሯቸው መሆኑን የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ከተዋዋይ ወገኖች ጋር ተባብረን መሥራታችንን እንቀጥላለን ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ደግሞ፣ የስምምነቱ ቀጣይ ተፈጻሚነት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡
/ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/