አዲስ አበባ —
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት አስመልክቶ በፓርላማ ማብራሪያ እንዲሰጡ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ማቅረቡን ኢዜማ አስታወቀ። የቀረበው ጥያቄ የመፍትሔ ሐሳብ አመላካችም እንደሆነ የፓርቲው ሊቀመንበር ተናገሩ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰመረ ሰሶ፤ የተጠቀሰው ደብዳቤ ለምክር ቤቱ መድረሱን ገልፀው በደብዳቤ ሊካተቱ ይገባቸው የነበሩ ነጥቦች እንዳሉ ለፓርቲው ሊቀመንበር ለአቶ የሺዋስ አሰፋ እንዳስታወቋቸውና የጎደለው ተሟልቶ ሲመለስ ለአፈ ጉባኤው እንደሚቀርብ ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡