በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ም/ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ ተጠሪዎች ማብራሪያ ሰጡ


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የባንክ፣ የመብራት እና የስልክ አገልግሎቶችን ኃላፊነት ወስዶ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚቸገር ገለጸ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ከሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት፣ ለእርዳታ አቅርቦት እና መሰል አገልግሎቶች ለሚደረግ በረራ፣ በተለይ ለተባበሩት መንግሥታት አውሮፕላኖች ፍተሻ ተደርጎባቸው የአየር ክልል እንደሚፈቀድላቸው አስታውቋል፡፡

ይሁን እንጂ አውሮፕላኖቹ ትግራይ ክልል ከደረሱ በኋላ ችግር ቢደርስባቸው መንግሥት ኃላፊነቱን እንደማይወስድ የተገለጸ ሲሆን ለየብስ ትራንስፖርትም መንግሥት ኃላፊነት እንደማይወስድ ተጠቁሟል፡፡ የተከዜ ድልድይ መሰበሩንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረጋግጧል፡፡

ከዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አካላት ጋር የተደረገውን ውይይት በንግግር የከፈቱት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን፣ የትግራይን ክልል ቀውስ ለመፍታት ሁሉን አቀፍ ውይይት ለማድረግ ፍኖተካርታ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ም/ጠ/ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ ተጠሪዎች ማብራሪያ ሰጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:25 0:00


XS
SM
MD
LG