በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ2014 ሁለተኛ ዙር ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ተጀመረ


የ2014 ሁለተኛ ዙር ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00

የ2014 ሁለተኛ ዙር ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ተጀመረ

የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ሁለተኛ ዙር ዛሬ መጀመሩን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የተቋሙ የኮሚኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለፁት፣ በሁለተኛው ዙር ለፈተና የተቀመጡት ከ354 ሺህ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው፡፡

በዩኒቨርሲቲዎች እየተሰጠ ባለው ፈተና ከመጀመሪያው ዙር ልምድ በመቅሰም፣ የዚህ ዙር አፈፃፀም የተሻለ እንዲሆንም ዝግጅት መደረጉን አመለወርቅ ህዝቅኤል ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮውን ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ 976 ሺህ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት ትግራይን ሳይጨምር 56 ሺህ ተማሪዎች ለፈተና እንደማይቀመጡ ታውቋል፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]

XS
SM
MD
LG