በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይና በህወሓት ጉዳይ የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋዜጣዊ ጉባዔዎች


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ሌ.ጄኔራል ባጫ ደበሌ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ሌ.ጄኔራል ባጫ ደበሌ

ከአሁን በኋላ በትግራይ ክልል ለሚፈጠሩ ችግሮች ኃላፊነቱን እንደማይወስድ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፣ መንግሥት ጦሩን ከትግራይ ያስወጣበትን ምክንያት ሲገልጹ ሚሳይል እና ሌሎች መሳሪያዎችን አውጥተናል እንደትናንቱ ሚያሰጋን ነገር የለም ብለዋል፡፡ በክልሉ ያለውን ጦር ማስወጣቱን የገለጸው መንግሥት፣ በቀጣይነት በክልሉ ስለሚፈጠሩ ጉዳዮች ተጠያቂው ህወሓት መሆኑን አስታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የኤርትራ ጦርም ከትግራይ ክልል ለቆ መውጣቱን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በበኩሉ የህወሓት ኃይል ሁመራና ራያን ጨምሮ በየትኛውም አቅጣጫ የመንቀሳቀስ ፍላጎት ካለው የከፋ አጸፋዊ እርምጃ እንደሚኖር አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል የተናጥል ተኩስ አቁም ስለማወጁ ከትናንት በስቲያ ያወጣውን መግለጫ በተመለከተ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ትናንት ከሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ መንግሥት ጦሩን ከትግራይ ያስወጣበትን ምክንያት ሲገልጹ ሚሳይል እና ሌሎች መሳሪያዎችን አውጥተናል እንደትናንቱ ሚያሰጋን ነገር የለም ብለዋል፡፡ በተያዘው ክረምት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ተግባራት መኖራቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በትግራይና በህወሓት ጉዳይ የፌዴራሉ መንግሥት ባለሥልጣናት ጋዜጣዊ ጉባዔዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:29 0:00


XS
SM
MD
LG