በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምሥራቅ ኢትዮጵያ የጫት ንግድ የቀን ኮታ ገደብ ወደ ቀድሞው መመለሱ ተገለጸ


በምሥራቅ ኢትዮጵያ የጫት ንግድ የቀን ኮታ ገደብ ወደ ቀድሞው መመለሱ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:17 0:00

በምሥራቅ ኢትዮጵያ የጫት ንግድ የቀን ኮታ ገደብ ወደ ቀድሞው መመለሱ ተገለጸ

ካለፈው መጋቢት ወር መባቻ አንሥቶ፣ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ በምሥራቅ ኢትዮጵያ የጫት ንግድ ላይ የጣለው የኮታ ገደብ፣ የጫት አምራች ገበሬዎችንና ነጋዴዎችን ለችግር ማጋለጡን ነዋሪዎች ተናገሩ።

ነዋሪዎቹ እንዳስረዱት፣ ከምሥራቅ ኦሮሚያ ዞኖች ወደ ሶማሌ ክልል በቀን የሚገባው ጫት፣ በፌዴራል መንግሥት ውሳኔ ወደ 17 ሺሕ ኪ.ግ. እንዲወርድ በመወሰኑ፣ የጫት ንግዱን በማቀዛቀዝ የበርካቶችን ኑሮ አናግቷል፡፡

የፌዴራል መንግሥት፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የበታች አካላት ጋራ አስፈላጊውን ምክክር ሳያደርግ ያሳለፈው ውሳኔ እንደኾነ የተቸው የምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ግብርና ቢሮ፣ ያስከተለው የገበያ እና የኑሮ መናጋት አፋጣኝ መፍትሔ እንደሚሻ አሳስቧል፡፡

የኦሮሚያ ንግድ ቢሮ በበኩሉ፣ ውሳኔው ቅራኔ በመፍጠሩ፣ ከፌዴራሉ መንግሥት ጋራ ምክክር ከተደረገ በኋላ፣ ትላንት ምላሽ መስጠቱን፣ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG