በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ


ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ውስጥ ለኮሮናቫይረስ የተጋለጡ ሰዎች ከፍተኛው ቁጥር ዛሬ መዘገበች።

ባለፉት 24 ሰዓታት ለ1 ሺህ 775 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 35 ሰዎች ኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አሳውቀዋል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ አብዛኛዎች የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ናቸው::

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድም በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ኮቪድ-19 እየተስፋፋ በመምጣቱ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ለአፍታም ሳይዘናጉ የወጡትን መመሪያዎች አጥብቀው እንዲተገብሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኮቪድ-19 በኢትዮጵያ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:19 0:00


XS
SM
MD
LG