በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"በምርጫው ዕለት ራሳችንን ከኮቪድ እንጠብቅ" የጤና ሚንስቴር


Dr. Lia Tadesse, Minister of Health of Ethiopia
Dr. Lia Tadesse, Minister of Health of Ethiopia

ከነገ ወዲያ ሰኞ በኢትዮጵያ በሚከናወነው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የሚሳተፉ ዜጎች ራሳቸውን ከኮቪድ19 ለመጠበቅ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደር ጉ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ።

ሀገር አቀፍ ምርጫው የኮቪድ19 ወረርሽኝ በዓለም አቀፍ እና በኢትዮጵያም እየተስፋፋ ባለበት ወቅት ላይ የሚካሄድ ምርጫ መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ ሁሉም ዜጋ በምርጫ ዕለት ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ብሏል።

በምርጫው ዕለት ዜጎች ወደ ምርጫ ጣቢያ ሲሄዱ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ /ማስክ መጠቀም፣ በመጨባበጥ እና በመተቃቀፍ ሰላምታ አለመለዋወጥ፣ ሰልፍ ላይ ወይም ማብራሪያ በሚሰጥ ጊዜ ከሌላው መራጭ ቢያንስ አንድ ሜትር ያህል ርቀትን መጠበቅ፣ እንዲሁም ንፁህ ውኃ ወይም የእጅ ማጽጃ ፈሳሽ በመጠቀም፣ የእጅ ንጽህናን መጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝቧል።

ከጤና ሚኒስቴር በሚወጣው ዕለታዊ የኮቪድ ይዞታ መረጃ መሰረት ፡ በሀገሪቱ እስከትናንት የኮቪድ አስራ ዘጠኝ መከላከያ የወሰደው ሰው ብዛት 1974476 ለቫይረሱ የተጋለጠው ሰው ብዛት 274 899 መሆኑ እና ከዚህ ውስጥ 253 634 ቱ ያገገሙ መሆናቸውን ሰንጠረዡ ያሳያል። በኮቪድ ምክንያት ህይወታቸውን ያጡት ደግሞ 4276 መሆናቸውን ከሰንጠረዡ ያገኘነው አሃዝ ይጠቁማል።

XS
SM
MD
LG