በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሃያ ሰባት ፓርቲዎችን ስረዘ


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሃያ ሰባት ፓርቲዎችን መስረዙን ይፋ አድርጓል። ቦርዱ እስከ መጋቢት 3/2012 ዓ.ም በቀድሞው ሕግ ሰርተፊኬት የነበራቸውና በቀድሞው ሕግ ምዝገባ ጀምረው ለነበሩ፣ 106 ፓርቲዎች በአዲሱ ሕግ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲያሟሉ ደብዳቤ ልኮ እንደነበረ አስታውሷል። ከመካከላቸው 76 ፓርቲዎች ሰነዶቹን ያቀረቡ መሆኑን እና ተሟልቶ መቅረቡ እየተመረመረ እንደሆን አውስቷል።

ሰነዶቻቸውን ማቅረብ ያልቻሉና ጊዜ እንዲራዘምላቸው ከጠየቁ አሥራ አምስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ አሥራ ሦስቱ አጥጋቢ ምክንያት ባለማቅረባቸው እንዲሰራዙ ተወስኗል ሲል የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ አስታውቋል። ሌሎች አሥራ አራት ፓርቲዎች ከእነአካቴው ሰነዶቻቸውን ያላቀረቡ፤ አንዳንዶች ከሌላ ፓርቲ ጋር የተዋሃዱ በመሆኑ ተሰርዘዋል ብሏል። ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ሰነድ ማቅረብ ያልቻሉት፣ በፓርቲው የውጭ ችግር የተነሳ መሆኑ ታምኖበት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሲያበቃ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን እንዲያካሂዱ መወሰኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ጨምሮ አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG