በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ላጋጠማት ችግር መፍትኄው “ሕገ መንግሥታዊ እንጂ ፖለቲካዊው አማራጭ አይደለም” - ብልጽግና ፓርቲ


የብልጽግና ፓርቲ ቃል አቀባይ አቶ አወሉ አብዲ
የብልጽግና ፓርቲ ቃል አቀባይ አቶ አወሉ አብዲ

ኢትዮጵያ ላጋጠማት ችግር መፍትኄው “ሕገ መንግሥታዊ እንጂ ፖለቲካዊው አማራጭ አይደለም” ብሏል ብልፅግና ፓርቲ።

የመፍትኄ ሃሳብ አለኝ የሚል ካለ “ከሕገ መንግሥታዊ ድንበር ሳይወጣ አማራጩን ማቅረብ ይችላል” ብለዋል የብልፅግና ፓርቲ ቃልአቀባይ አቶ አወሉ አብዲ ከቪኦኤ ጋር ቃለምልልስ ሲያደርጉ።

በሚቀርቡ አማራጮች ላይ ከማንም ጋር ለመወያየት ፓርቲያቸው ዝግጁ መሆኑን ያሳወቁት አቶ አወሉ “በውይይት እና በድርድር ስም ጫና ለመፍጠር ማሰብ ተቀባይነት የለውም፤ ከሕገ መንግሥታዊ አማራጮች ውጪ ሌላ መንገድ በመጠቀም፣ በአቋራጭ ሥልጣን ለመያዝ የሚያስብ ካለ ግን መንግሥት ሕገ መንግስቱን ለመጠበቅ ሲል ህጋዊ እርምጃ ይወስዳል” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢትዮጵያ ላጋጠማት ችግር መፍትኄው “ሕገ መንግሥታዊ እንጂ ፖለቲካዊው አማራጭ አይደለም” - ብልጽግና ፓርቲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:19 0:00


XS
SM
MD
LG