በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ትንታኔ “ያልተገባ ንጽጽር” እንደታየበት ባለሞያዎች ተቹ


የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ትንታኔ “ያልተገባ ንጽጽር” እንደታየበት ባለሞያዎች ተቹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:40 0:00

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ትንታኔ “ያልተገባ ንጽጽር” እንደታየበት ባለሞያዎች ተቹ

“የአገር ውስጥ የኢኮኖሚ እና የገበያ አመራር የተዛባ ነው ወይስ ሚዛናዊ የሚለውን በግልጽ መፈተሽ ይገባል” - ዶር. አክሎግ ቢራራ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ/ዶር./፣ ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የሰጡት ማብራሪያ፣ “ከእውነታው የራቀ እና የአገር ውስጥ ወቅታዊ ኹኔታን ያላገናዘበ ነው፤” ሲሉ፣ ኹለት የንግድ እና የኢኮኖሚ ባለሞያዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ፡፡

የንግድ እና የምጣኔ ሀብት ባለሞያዎቹ ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እና ዶ/ር አጥላው ዓለሙ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እየጨመረ የመጣውን የዋጋ ግሽበት እና መንሥኤውን፣ ከዓለም አቀፉ ኹኔታ ጋራ ማያያዛቸው ትክክል አለመኾኑን ተናግረዋል፡፡

በዐዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የምጣኔ ሀብት መምህር የኾኑት ዶ/ር አጥላው ዓለሙ፣ የዋጋ ግሽበቱ ከዛሬ 18 ዓመት በፊት አንሥቶ እየጨመረ የመጣ ቢኾንም፣ እንዲህ እንደ አኾኑ ኾኖ አያውቅም፤ ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፍ ኹኔታው፣ ግሽበቱን የሚያባብስበት ተያያዥነት ሊኖረው ቢችልም፣ የዋጋ ንረቱ፥ ከኮቪድ 19ም፣ ከዩክሬኑም ኾነ ከአገር ውስጥ ጦርነቶች በፊት እንደነበረ ዶ/ር አጥላው ጠቅሰዋል፡፡

ኹሉንም ነገር ከውጭ ኹኔታ ጋራ የማያያዙ ነገር “ሰልችቶኛል” ያሉት፣ የዓለም ባንክ የረጅም ጊዜ የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት ዶ/ር አክሎግ ቢራራም፣ ታላላቅ ኢኮኖሚ ያላቸው አገሮች ኢኮኖሚ እና ባንኮቻቸው ችግር ላይ ናቸው፤ የሚለው የጠቅላይ ሚኒስትሩ አገላለጽ፣ ያልተገባ ንጽጽር መኾኑን አስረድተዋል፡፡ ይልቁንም፣

ዶ/ር አክሎግ የአገር ውስጥ የኢኮኖሚ እና የገበያ አመራር የተዛባ ነው ወይስ ሚዛናዊ የሚለውን በግልጽ መፈተሽ እንደሚገባ መክረዋል ፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG