በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከጎረቤት ሃገራት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን መንግሥትን ወቀሱ


በጂጂጋ ለይቶ ማቆያ ያሉ ከጎረቤት ሃገራት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገልን አይደለም ሲሉ ወቀሱ። ማስክና ሳሙና አልተሰጠንም፣ በአንድ ክፍል ከ3 እስከ 6 ሆነን እንድንኖር እንደረጋለን፣ ከኮሮና ቫይረስ ነጻ ከሆንን በኋላም እንድንሄድ አልተደረግንም፣ የምግብና መጠጥ አቅርቦቱም ችግር ያለበት ነው ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

የሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ በበኩሉ ክፍተቶች ቢኖሩም የተወራውን ያህል አይደለም ብሏል። በዛሬው ዕለት አራት መቶ አሥራ አንዱ ዛሬ ከለይቶ ማቆያ ወጥተው ወደየትውልድ አካባቢያቸው ይሄዳሉ ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከጎረቤት ሃገራት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን መንግሥትን ወቀሱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:42 0:00


XS
SM
MD
LG