ዋሽንግተን ዲሲ —
ባለፈው ሳምንት አርብ ጥቅምት 26/2014 ዓ.ም ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ መግለጫ የሰጡ የፖለቲካ ድርጅቶች ህወሓትና ኦነግን ጨምሮ ዘጠኝ ሆነው የኢትዮጵያ ፌዴራሊስትና ኮንፌደራሊስት ኃይሎች ጥምረት በሚል መመስረታቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ጥምረቱ በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት በኃይል በማውረድ የሽግግር ሂደት እንዲኖር ለማድረግ እንደሚሠራም ይፋ አድርገዋል። በዚህ ጉዳይ ሁለት እንግዶችን አነጋግረን ዘገባ አሰናድተናል። አቶ ዩሃንስ አብርሃ የቀድሞ ዲፕሎማት ሲሆኑ አሁን ካናዳ ይገኛሉ። የትግራይ ክልላዊ መንግሥትን በመወከል በውጭ አገር እንቅስቃሴ የሚያደርግ ኮሚቴ ጋር አብረው በመሥራት ላይ ይገኛሉ። የጥምረቱ አስተባባሪ መሆናቸውንም ገልፀዋል።
አቶ ውብሸት ሙላት የሕግ ምሑር ናቸው። በተለያዩ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ አስተያየት በመስጠት ይታወቃሉ። በጥምረቱና ተያያዠ በሆኑ ጉዳዮች የሁለቱን አስተያየት ጠይቀን ለቅዳሜ ምሽት የውይይት ፕሮግራማችን አሰናድተነዋል።
ክፍል አንድን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ