በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ውጊያ እንዲቆም ፖምፔዮ ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ

ኢትዮጵያ ውስጥ ጦርነት ሙሉ በሙሉ እንዲቆም የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ጠይቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ትናንት ባወጡት የትዊተር መልዕክት ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውንና ትግራይ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ውጊያ ሙሉ በሙሉ እንዲቆም የጠየቋቸው መሆኑን ገልፀዋል።

“ንግግር እንዲጀመር፣ ነፃ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታና አገልግሎቶች አቅርቦት እንዲኖር” ጠይቄአለሁ ብለዋል ፖምፔዮ በዚሁ ትዊታቸው።

የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች እንደተቋረጡ በመሆኑ ክልሉ ውስጥ ያሉ ሁኔታዎችን በቅርበት ለማወቅ አልተቻለም።

በሌላ በኩል ግን 43 ሺህ ኢትዮጵያዊያን ግጭቱን ሸሽተው ሱዳን መግባታቸውን ያስታወቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኛ ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር /ዩ ኤን ኤች ሲ አር/ ለስደተኞቹ እርዳታ ማቅረብ የሚያስችለው የ147 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዲደረግለት ጠይቋል።

በሌላ በኩል በህወሃት ቁጥጥር ሥር ነበሩ የተባሉ ከአንድ ሺህ አንድ መቶ በላይ የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት ወደ አማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መግባታቸውን የዞኑ የመንግሥት ኮምኒኬሽንስ ጉዳዮች መምሪያ አስታውቋል።

ወደ ዞኑ ከገቡት ውስጥ በጦርነቱ የቆሰሉ፣ እንዲሁም በረሃብና በህመም የተዳከሙ እንደሚገኙባቸው
የመምሪያው ኃላፊ ጳውሎስ በላይ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

XS
SM
MD
LG