አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል እያካሄደ እንዳለ የሚገልፀው የህግ ማስከበር ዘመቻ ፍፃሜውን ሊያገኝ መዳረሱን አስታወቀ።
የዘመቻው ማጠናቀቂያ በሆነችው መቀሌ ከተማና ነዋሪዎቿ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የሚቻለው ጥንቃቄ ሁሉ እንደሚደረግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፁ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ የፌዴራል መንግሥት በተቆጣጠራቸው የትግራይ ክልል አካባቢዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አመለከተ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡