በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዐማራ ክልልን በመቆጣጠር የፌዴራል መንግሥቱን ለመጣል በኅቡእ ተደራጅተዋል የተባሉ ግለሰቦች ዝርዝር ይፋ ተደረገ


ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሓይል ለማፍረስ እና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ
ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በሓይል ለማፍረስ እና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የሚፈለጉ

- "ኅቡእ አደረጃጀቱን አናውቀውም፤ ግንኙነትም የለንም" - /አቶ ልደቱ አያሌው እና አቶ ሀብታሙ አያሌው/

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የጸጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል፣ በቁጥጥር ሥር እንዳዋላቸው ገልጾ ስማቸውንና ምስላቸውን ይፋ ከአደረጋቸው ተጠርጣሪዎች የሚበዙቱ፤ ሁከት እና ብጥብጥ በመፍጠር ወንጀል፣ የተወሰኑቱ ደግሞ በግብረ ሽብር ተጠርጥረዋል ተብለው በፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ናቸው፡፡

በተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት ከተጠረጠሩት ግለሰቦች መካከል፣ የዋስ መብታቸው ከተፈቀደላቸው በኋላ በግብረ ሽብር ዐዲስ ክሥ የተከፈተባቸው መኖራቸውን፣ ከጠበቆቻቸው አንዱ የሕግ አማካሪ እና ጠበቃ ሰሎሞን ገዛኸኝ ሲገልጹ፣ የሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ጉዳይም ወደዚኹ ክሥ ሊቀየር እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡

ለሽብር ተልዕኮ በኅቡእ አደረጃጀት ውስጥ ተገኝተዋል፤ ከተባሉ ታዋቂ ግለሰቦች መካከል፣ አቶ ልደቱ አያሌው እና ከሀገር ውጭ የሚኖሩ የብዙኀን መገናኛ ባለሞያዎችም የተጠቀሱ ሲሆን፣ ወደ ሀገር ቤት ተላልፈው እንዲሰጡት ከዓለም አቀፍ የሕግ አካል ጋራ እየሠራ መኾኑን ግብረ ኃይሉ አስታውቋል፡፡

ከዚኹ የጋራ ግብረ ኃይሉ መግለጫ ጋራ በተያያዘ፣ "በኅቡእ አደረጃጀት አሉበት" በሚል ስማቸው ከተጠቀሱት መካከል፣ የአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው ታዋቂው ፖለቲከኛ አቶ ልደቱ አያሌው እና የኢትዮ 360 የሥራ ሒደት ሥራ አስኪያጅና የፖለቲካ ተንታኝ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ ውንጀላው ከሰላማዊ አቋማቸውና ከሞያ ተልዕኳቸው ጋራ እንደሚፃረር ገልጸዋል። የተባለውን ኅቡእ አደረጃጀት እንደማያውቁትና ከተዘረዘሩት ግለሰቦች ጋራም ግንኙነት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

የዚህን ዘገባ ሙሉ ዝርዝር ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG