የፌዴራል መንግሥቱና የህወሐት ዋና ተደራዳሪዎች ደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ ውስጥ የሠላም ሥምምነት ከተፈራረሙና ናይሮቢ ኬንያ ውስጥ የትግበራ ሠነድ ላይ ፊርማቸውን ካኖሩ በኋላ የተለያየ እርዳታ የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል እየደረሱ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች በመግለፅ ላይ ናቸው።
በሌላ በኩል ሰሞኑን ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጡት የክልሉ የግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አትንኩት መዝገቡ ከሥምምነቱ ወዲህ ከ36 ሺሕ ኩንታል በላይ እህል ወደ ትግራይ መግባቱ ገልፀው ነገር ግን መጠኑ ከሚያስፈልገው በእጅጉ ያነሰ ነው ብለዋል።
የሕፃናት አድን ድርጅት የእርዳታ እህል በማድረስ ላይ ከሚገኙት ረድዔት ድርጅቶች አንዱ ሲሆን ከሥምምነቱ ወዲህ የተሻለ ሁኔታ በመፈጠሩ እርዳታ ለተጎጂዎች ማድረሱን ገልጿል።
አሁንም ግን የበለጠ መሻሻል የሚገባቸው ጉዳዮች እንዳሉ ጠቁሟል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ /