ዋሺንግተን ዲሲ —
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ መርክል ጋር በስልክ መወያየታቸውን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ጠቆሙ።
ኮቪድ-19ን ለመከላከልና ሥርጭቱን በመግታት ላይ ያተኮረ ውይይት ማድረጋቸው፤ ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ ስለለገሰችው የኮቪድ-19 መመርመሪያ ግብዓትና መገልገያ ቁሳቁሶች፤ በዚህ ፈታኝ ወቅትም ጀርመን ከኢትዮጵያ ጎን ለመቆም ያላትን ቁርጠኝነት እና አጋርነት ማሳየቷን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ማመስገናቸውን ጠቅሰው የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርክል የታላቁን የኅዳሴ ግድብ አስመልከቶ ለሁሉም አካላት የሚያመች ሥምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን እንደሚደግፉም በውይይታቸው ገልፀዋል።