በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጠ/ሚ ዐቢይ የአስመራ ጉብኝት


ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የጋሽ ባርካ ከርከበት ግድብና አካባቢ ያሉትን የግብርና ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የጋሽ ባርካ ከርከበት ግድብና አካባቢ ያሉትን የግብርና ልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአስመራ ያደረጉትን የሁለት ቀናት ጉብኝት አጠናቀው ትናንት ዕሁድ ወደአዲስ አበባ ተመልሰዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቅዳሜ ዕለት በስፋት ባደረጉት ውይይት በሁለቱ ሃገሮች መካከል ታሪካዊ የሰላምና የወዳጅነት ሥምምነት ከተፈረመ ወዲህ የተመዘገቡ እርምጃዎችን እና ያጋጠሙ እንቅፋቶችን በስፋት መገምገማቸውን የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና አብረዋቸው የተጓዙት ልዑካን ከፕሬዚዳንት ኢሳያስና ከሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ሆነው በጋሽ ባርካ ከርከበት ግድብና አካባቢ ያሉትን የግብርና ልማት ፕሮጀክቶች መጎብኝተቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG