በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሠራዊቱ ባለበት እንዲቆም ታዘዘ


ፎቶ ፋይል፦ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ
ፎቶ ፋይል፦ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ

የመከላከያ ሠራዊት በምሥራቅ አማራና አፋር ክልሎች ከህወሓት ቁጥጥር ነፃ ያወጣቸውን አካባቢዎች አፅንቶ እንዲቆይ መታዘዙን መንግሥት አስታወቀ።

ትዕዛዙ የተላለፈው በሦስት ምክንያቶች መሆኑን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ አገልግሎት ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ከነዚህም መካከል ከዚህ በፊት በትግራይ ክልል ካጋጠሙት ችግሮች ትምህርት በመውሰድ መሆኑን አብራርተዋል።

ይህንንም ሲያስረዱ "የትግራይ ክልል የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ ቀደም ሠራዊቱን ከኋላ ወግተዋል" ብለዋል።

ሚኒስትሩ አክለውም "ዘመቻ ለኅብረብሄራዊ አንድነት በአሸባሪው ኃይል የተወረሩ አካባቢዎችን ነፃ በማውጣት የመጀመሪያውን ግብ አሳክቷል፤ በዚህም ተልዕኮውን አጠናቅቋል" ብለዋል።

ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በመንግሥቱ መግለጫ ዙሪያ ከህወሓት ወገን የተሰጠ ቀጥተኛ ምላሽ የለም።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ሠራዊቱ ባለበት እንዲቆም ታዘዘ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:40 0:00


XS
SM
MD
LG