በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በኤርትራ ባለሥልጣን ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች


ዩናይትድ ስቴትስ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ተገድለውበታል፣ ከ 2 ሚሊዮን በላይ ተፈናቅለውበታል በተባለው፣ የኢትዮጵያው ትግራይ ክልል ግጭት፣ በተፈጸመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰት ተሳትፈዋል፣ በሚል በተከሰሱት የኤርትራ ባለስልጣን ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታውቃለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትት የገንዘብ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፣ የኤርትራን መከላከከያ ሠራዊት፣ የጦር ኃይሎች አዛዥ ፊሊፖስ ወ/ዮሀንስ በጅምላ ፍጅት፣ በጾታ ጥቃት፣ እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን በመንገድ ላይ ሆን ብለው እንዲገደሉ በማድረጋቸው እና በሌሎች የሰአብዊ መብት ጥሰቶች በመክሰስ በጥቁር መዝገብ እንዲመዘገቡ ያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ገንዘብ ሚኒስቴር የውጭ ይዞታና ንብረቶች ቁጥጥር ድሬክተር አንድርያ ጋኪ ባወጡት መግለጫ “የዛሬው እርምጃ ዩናይትድ ስቴትስ ለእንዲህ ዓይነት አስነዋሪ ድርጊት ተጠያቂ በሆኑና ግጭቱ እንዲባባስ በማድረግ ኢትዮጵያውያን ወደ ሰቆቃ እንዲያመሩ ያደረጉ ወገኖችን ዋጋ ለማስከፈል ያላትን ቁርጠኝትነ ያሳያል ብለዋል፡፡

ጋኪ በመግለጫቸው “ ኤርትራ በአስቸኳይና በዘላቂነት ኃይሎችዋን ከኢትዮጵያ እንድታስወጣ ሁሉም ወገኖች የተኩስ አቁም አድርገው መነጋገር እንዲጀምሩና የሰአብ አዊ መብጥ ጥሰቱ እንዲቆም እናሳስባለን “ ብለዋል፡፡

ዩናይናይትድ ስቴትስ የኤርትራ ሠራዊት ትግራይ ለቆ እንዲወጣ በተደጋጋሚ ስታስታውቅ መቆየትዋም ተመልክቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ ውስጥ ተፈጽመዋል ከተባሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ጋር በተያይዘ የኡናይትድ ስቴትስ በኤርትራ የመከላከያ ኃይሎች ጠቅላይ ማዦር ሹም ጀኔራል ፊሊጶስ ወልደዮሀንስ ላይ ማዕቀብ መጠሏን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማዕቀብ መጣሏን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ዛሬ ባወጡት መገልጫ አሳውቀዋል፡፡

ማዕቀቡ በጀኔራል ፊሊጶስ ላይ የተጣለው የዩናይትድ ስቴትስ በከበዱ የሰብዓዊ መብት ረገጣዎችና በሙስና በዓለም ዙሪያ ተጠያቂ ናቸው በሚባለው ድንጋጌ መሠረት መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አመልከተዋል፡፡

በሌላም በኩል ግን ይህን የዩናይትድ ስቴትስን እርምጃ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል የኤርትራ መንግስት ኮንኗል፡፡

የኤርትራ መንግሥት "ደብዳቤውንም ሆን የደብዳቤውን መፈንስ ፈፅሞ መሠረተ ቢስና ኤርትራን ለማሸማቀቅ የታሰበ ነው" ሲል የጠራው ሲሆን እንደማይቀበለውም አስታውቋል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

አሜሪካ በኤርትራ ባለሥልጣን ላይ ማዕቀብ መጣሏን አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:20 0:00XS
SM
MD
LG