በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራውያን ስደተኞች አዲስ አበባ ውስጥ ሰልፍ አካሄዱ


ኤርትራውያን ስደተኞች አዲስ አበባ ውስጥ ሰልፍ አካሂዱ
ኤርትራውያን ስደተኞች አዲስ አበባ ውስጥ ሰልፍ አካሂዱ

በብዙ መቶዎች የተቆጠሩ ኤርትራውያን ስደተኞች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ሰልፍ አካሂደዋል።

ኤርትራውያኑ ስድተኞች የተመድ የስድተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር "በትግራይ በውጊያ የተጠመዱትን በሁለት ካምፖች የተጠለሉ ጓደኞቻችንን እና ቤተሰቦቻችንን አውጥቶ ወደሌላ ቦታ ያዛወርልን" ሲሉ መጠየቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ በተባሉት ካምፖች ውስጥ እና ዙሪያው ውጊያው እየተባባሰ መሆኑን ያመለከተው ዘገባው ዩኤንኤችሲአር በቅርቡ ሁለት ስደተኞች መገደላቸውን መናገሩን አክሏል።

የመንግሥታቱ ድርጅት የስድተኞች ኮምሽን እአአ ከሃምሌ 14 ወዲህ ካምፖቹ ጋ መድረስ እንዳልቻለ ጠቅሷል።

ባለፈው ማክሰኞ ዩናይትድ ስቴትስ ትግራይ ውስጥ ያሉት ኤርትራውያን ስደተኞች ጉዳይ በጥልቅ እንዳሳሰባት አስታውቃለች።

አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደው የስደተኞቹ ሰልፍ ላይ ከተካፈሉት መካከል አንዱ የሆነው ሄርሞን ሃይሉ

ማይ አይኒ መጠለያ ካምፕ ያሉትን እናቱን ለሳምንታት በስልክ ሊያገኛቸው እንዳልቻለ እና እንደተጨነቀ መግለጹን ሮይተርስ ዘግቧል።

ማክሰኞ ዕለት ዩኤንኤችሲአር ከሁለቱ የኤርትራውያን ስደተኞች መጠለያዎች አንድ መቶ የሚሆኑ ስደተኞች አውጥቶ ወደሌላ ቦታ ማዛወሩ እና የተቀሩትንም ደህንነታቸው ተጠብቆ የሚወጡበትን መንገድ ለማመቻቸት ከክልሉ ባለልስልጣናት ጋር እየተነጋገርን ነን ሲል ማስታወቁን ዘገባው አክሏል።

በዛሬ አዲስ አበባ ላይ በተካሄደው የኤርትራውያን ስደተኞች ሰልፍ ጉዳይ ዘገባው የዩኤን ኤች ሲ አርን አስተያየት አግኝቶ ለማካተት እንዳልቻለ ሮይተርስ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG