ኤርትራ ነፃ የወጣችበትን 31ኛውን የነጻነት ቀን ዛሬ አክብራለች፡፡ በተለይ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወቂ፣ ዲፕሎማቶችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና እንግዶች በተገኙበት በአስመራ ስቴዲዮም በተካሄደው ስነ ሥርዓት በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩ ተገለጿል፡፡
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ በፕሮግራሙ ላይ ባሰሙት ንግግር ይህችን እለት ለመጎናጸፍ በርካታ ረጅም አስቸጋሪ የትግል ሂደቶች መታለፋቸውን ገልጸዋል፡፡
አሁን በዓለም አቀፍ ሁኔታ እየተፈጠረ ያለው ችግርም ምዕራባውያን ዓለም ለመቆጣጠርና ፈቃዳቸውን የማይፈጽሙት ሌሎችን አገሮች ለማስገበር ካላቸው ፍላጎት የመነጨ ነው ብለዋል፡፡
በሩሲያ የተፈጠረውም ተመሳሳይ ነገር መሆኑን ጠቅሰው በቻይናም ይህ የሚቀጥል መሆኑን በምሳሌነት አንስተዋል፡፡