በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድና ኢሳያስ አፈወርቂ ዘርፈ ብዙ ሥምምነት ተፈራረሙ


የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያው አቻቸው ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድ።
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያው አቻቸው ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድ።

ኤርትራና ሶማሊያ የመከላከያ፣ የድኅንነት፣ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ትብብር ሥምምነት መፈራረማቸውን ትናንት ማክሰኞ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያው አቻቸው ሐሰን ሼኽ ሞሃሙድ ሥምምነቱን የተፈራረሙት ፕሬዚዳንት ሞሃሙድ ኤርትራ ውስጥ ያደረጉትን የአራት ቀናት የሥራ ጉብኝት ትናንት ሲያጠናቅቁ ነው።

ኤርትራ የሶማሊያ ወታደሮችን ወደ ሦስት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ እያሠለጠነች እንደሆነ ይታወቃል።

በኤርትራ እየሠለጠኑ ያሉት የሶማሊያ ወታደሮች ቁጥር 5ሺ167 መሆኑን ወታደሮቹን ለሥልጠና የላኳቸው የቀድሞው ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፎርማጆ መግለፃቸውን የቪኦኤ የሶማልኛ ክፍል ዘግቧል።

ሥልጠናው ከህዝብና ከመገናኛ ብዙኃን የተደበቀ መሆኑና ፕሮግራሙ በሶማሊያዊያን የወታደሮቹ ወላጆችና ፖለቲከኞች በኩል ተቃውሞ የቀረበበት እንደነበር ተገልጿል።

ወታደሮቹ “ትግራይ ውስጥ በተካሄደው ጦርነት ውስጥ ተሰልፈዋል” በሚል የተሠራጨ ያልተረጋገጠ ዘገባ ላይ የሶማሊያ መንግሥት ብርቱ ማስተባበያ ሰጥቶበታል።

የቪኦኤ ሶማሊኛ ዝግጅት ክፍል ወታደሮቹ በትግራይ ጦርነት ስለመሣተፋቸው ማረጋገጫ አለማግኘቱን አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG