በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚዳንት ኢሣያስ ለሥራ ጉብኝት ግብፅ ናቸው


የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂና የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደልፋታህ አል ሲሲ
የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂና የግብፅ ፕሬዚዳንት አብደልፋታህ አል ሲሲ

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ ትናንት ዕሁድ ለሥራ ጉብኝት ወደግብፅ ተጉዘዋል።

ፕሬዚዳንቱ በካይሮ የሦስት ቀናት ቆይታቸው ከግብፅ ፕሬዚዳንት አብደልፋታህ አል ሲሲ እና ከሌሎችም የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ጋር በሁለቱ ሃገሮች ጉዳዮች እንዲሁም የሁለቱም ሃገሮች ትኩረት በሆኑ ክልላዊ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚወያዩ ከኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ከፕሬዚዳንት ኢሣያስ ጋር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ኦስማን ሳልህ እና ፕሬዚዳንታዊ አማካሪ የማነ ገብረአብ አብረዋቸው መጓዛቸውንም ገልጿል።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ባለፉት ቅርብ ሳምንታት በኢትዮጵያና በሱዳን ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸውን የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ መግለጫ አስታውሷል።

XS
SM
MD
LG