በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቻይና ቴሌኮም በዩናይትድ ስቴትስ እንዳይሰራ ታገደ


የቻይና ቴሌኮም
የቻይና ቴሌኮም

የዩናይትድ ስቴትስ የፌደራል ኮሚኒኬሽን ኮሚሽን/FCC/ በቻይና መንግሥት የሚተዳደረው የቻይና ቴሌኮም ኩባንያ፣ በብሄራዊ የደህንነት ስጋት ሳቢያ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሠጠውን የሥራ ፈቃድ መንጠቁን ትናንት ማክሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

በዩናይትድ ስቴትስ የስልክ፣ የዋይረለስ እና የቪዲዮ ግንኙነቶችን የሚቆጣጠረው ኮሚሽን ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ላለፉት 20 ዓመታት ሲሰራ የቆየው፣ "ቻይና ቴሎኮም አሜሪካ" በሚቀጥሉት 60 ቀናት ውስጥ፣ ሥራውን እንዲያቋርጥ አዟል፡፡

ኮሚሽኑ በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚንቀሳቀሰው ድርጅት በሚሰጠው አገልግሎት “ለብሄራዊ ደህንነት እና ህግ ማስከበር አሳስቢ ስጋቶችን ፈጥሯል” ብሏል፡፡ ድርጅቱ “በዩናይትድ ስቴትስ የሚደረጉ ግንኙነቶችንና ልውውጦችን በማግኘት፣ በመመዝገብ፣ በማወክና በመጠቀም ወይም አቅጣጫቸውን በማስቀየር፣ እንዲሁም፣ መልሶ ደግሞ እነሱን በመጠቀም ዩናትይትድ ስቴትስን በሚጎዱ የስለላ ተግባራት ይጠቀምበታል” ብሏል፡፡ በቻይና ትልቁ የቴሌኮሙኒኬሽን ድርጅት የሆነው የቻይና ቴሌኮም ቃል አቀባይ የኮሚሽኑ ውሳኔ “አሳዛኝ ነው” ካለ በኋላ “ደንበኞቻችንን መልሰን ለማገለገል ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን” ብሏል፡፡ ውሳኔው በቀድሞው ፕሬዚዳን ትራምፕ ዘመን በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መሠረታቸውን ቻይና ባደረጉ ድርጅቶች የሚደረገውን የቴሌክኖሎጂና ገበያ መስፋፋትን ለመገደብ የተጀመረው እርምጃ አካል መሆኑን ተመልክቷል፡፡ የቻይናው ህዋዌ ባለፈው ዓመት የሚሰጠውን የ5ጂ አገልግሎት በመጠቀም የዩናትድ ስቴትስ መረጃዎችን ዘንድ እንዳይደርስ አግዷል፡፡

XS
SM
MD
LG