በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቻድ በተደረገ ተቃውሞ ቢያንስ 60 ሰዎች ተገደሉ


የቻድ ተቃውሞ
የቻድ ተቃውሞ

በቻድ የሃገሪቱ ግዜያዊ መሪ የሥልጣን ዘመናቸውን በሁለት ዓመት ማሥረዘማቸውን ተከትሎ በሁለት ታላላቅ ከተሞች በተደረገ የተቃውሞ ልፍ የፀጥታ ኃይሎች ተኩስ ከፍተው 60 ሠዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ከመንግሥት ቃል አቀባይ እንዲሁም ከአስከሬን ማቆያ ሥፍራዎች የተገኘው መረጃ ያሳያል።

እንደ አሶሲዬትድ ፕረስ ዘገባ ከሆነ ሁከቱን ተከትሎም ባለሥልጣናት የሰዓት እላፊ ገደብ ደንግገዋል።

የማዕከላዊቷ አፍሪካ ሀገር ግዜያዊ መሪ ማሃማት እድሪስ ዴቢ በሁለት ዓመት ሥልጣናቸውን ማራዘማቸውን ተከትሎ ነው ተቃዋሚዎች ወደ ጎዳና የወጡት።

የማሃማት እድሪስ ዴቢ አባት ለሦስት አስርት ዓመታት ከገዙ በኋላ ባለፈው ዓመት በነፍሰ ገዳይ ጥይት ህይወታቸው እሲኪያልፍ፣ በቻድ ብዙም ተቃውሞ አይሰማም ነበር።

ፈረንሳይ፣ የአፍሪካ ኅብረትና ሌሎች ወገኖች የፀጥታ ኃይሎች በሠልፈኞች ላይ የወሰዱትን እርምጃ ወዲያውኑ አውግዘዋል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የምዕራብና መካከለኛው አፍሪካ ኃላፊ ሳሚራ ዳውድ፣ የቻድ ባለሥልጣናት በተቃዋሚዎች ላይ የሚጠቀሙትን ከመጠን ያለፈ ኃይል ከመጠቀም እንዲገ'ቱ ጥሪ አቅርበዋል።

የቻድ መንግሥት ቃል አቀባይ አዚዝ ማሃማት ሳለኽ በበኩላቸው በዋና ከተማይቱ እንጃሜና ብቻ ቢያንስ መገደላቸውን አመልክተዋል።

የሠልፉ አስተባባሪዎች ግን የሟቾቹ ቁጥር 40 ነው ይላሉ። በጥይት የተጎዱ በርካታ ሰዎች አሉም ነው የሚሉት። የሚወጡትን አሃዞች በገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ እንዳልቻለ የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

በቻድ ሁለተኛ ከተማ ማውንዶ 32 ሰዎች መገደላቸውን አንድ የከተማው የአስከሬን ማቆያ ሠራተኛ አስታውቀዋል። ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉት እኚህ ግለሰብ 60 ሰዎች እንደተጎዱም ተናግረዋል።

በሌሎች ሁለት ከተሞችም ተቃውሞ እንደነበር የአሶሲዬትድ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG