በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካናዳ ከባድ የጭነት ማመላለሻ አሽከርካሪዎች አሁንም ድንበሩን እንደዘጉ ነው


በካናዳ የኮቪድ-19 የጤና ህግጋትን በመቃወም የተካሄደ ሰልፍ
በካናዳ የኮቪድ-19 የጤና ህግጋትን በመቃወም የተካሄደ ሰልፍ

በካናዳ የኮቪድ-19 የጤና ህግጋትን በመቃወም የተጀመረው እና ወደ ሌሎች አካባቢዎችም እየተዛመተ ያለው በከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የተመራ እንቅስቃሴ፣ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚያስገባ እና ከዩናይትድ ስቴትስ የሚያስወጣውን የድንበር መተላለፊያ መዝጋት ተከትሎ ዋሽንግተን በሁለቱ አገሮች የጋራ ድንበር ላይ የተፈጠረውን ሁኔታ እንዲስተካከል ትናንት የካናዳ መንግሥት ፌዴራል ኃይሎች መተላለፊያውን በዘጉት ወገኖች ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ስትል በስተሰሜን የምታዋስናትን ጎረቤቷን ጠየቀች።

የካናዳይቱን ኦንታሪዮን እና የዩናይትድ ስቴትሷን ዲትሮይትን ከተማ የሚያገናኘው እና “አምባሳደር ድልድይ” በመባል የሚታወቀው ቁልፍ መተላለፊያ ለቀናት መዘጋቱን ጨምሮ የድንበር መተላለፊያዎቹ ለቀናት መዘጋት በንግድ እንቅስቃሴው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተዘገበ።

ዋና ዋና የአውቶሞቢል ሰሪዎች በዚህ ሳቢያ በበርካታ ፋብሪካዎች የምርታቸውን መጠን ለመቀነስ መገደዳቸው ታውቋል።

በምዕራብ ካናዳይቱ ግዛት አልበርታም ሁለተኛ ዋና የድንበር መተላለፊያ ለቀናት እንደተዘጋ ሲሆን፤ ትናንት ሃሙስ ሌላ ሶስተኛ መተላለፊያም በማዕከላዊ ማኒቶባ ዘግተዋል።

XS
SM
MD
LG