በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቡርኪና ፋሶ ውስጥ በደረሰ ጥቃት 60 ሰዎች ተገደሉ


ቡርኪና ፋሶ ውስጥ ባለፈው ሳምንት የጦር ሠራዊቱን መለዮ ልብስ የለበሱ አጥቂዎች ስድሳ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸው ተገለጠ፡፡ ሰሜናዊ ቡርኪና ውስጥ ጥቃቱ መድረሱን የአካባቢው አቃቤ ህግ የፖሊስ ሪፖርት ጠቅሰው ተናግረዋል፡፡

ያቴንጋ በሚባለው እና ማሊ አቅራቢያ በሚገኘው የቡርኪና ፋሶ ክፍለ ሀገር ውስጥ ስለደረሰው ግድያ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አቃቤ ህጉ አመልክተዋል፡፡

በአካባቢው በተጠርጣሪ ጂሃዲስቶች የሚፈጸሙ ተመሳሳይ ጥቃቶች እየተደጋገሙ መጥተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG