በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወታደሮቹ ቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ ግልበጣው ያለምንም ደም መፋሰስ መካሄዱን ተናገሩ


የነዋሪች ሰልፍ በኦጋዱጉ ቡርኪና ፋሶ
የነዋሪች ሰልፍ በኦጋዱጉ ቡርኪና ፋሶ

የቡርኪና ፋሶ ወታደሮች ፕሬዚዳንት ሮክ ማርክ ክሪስቲያንን ኮብሬን ማስወገዳቸውን የገለጹ ሲሆን አሁን አገሪቱን እየተቆጣጠረ የሚገኘው ወታደራዊ ጁንታ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ትናንት ሰኞ በመንግሥት ቴሌቪዥን የቀረቡ በርካታ ወታደሮች ግልበጣው የተካሄደው ያለምንም ደም መፋሰስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ካፕቴን ሲድሶሬ ካብሬ አዲሶቹ ወታደራዊ መሪዎች በሁሉም ወገኖች ተቀባይ የሆነው አዲስ ምርጫ የሚካሄድበት ወቅት እንደሚያሳውቁ ተናግረዋል፡፡

የወታደሮቹ እምርጃ የመጣው የቡርኪና ፋሶ ህዝብ የፕሬዚዳንቱ አስተዳደር የእስላማዊ አማጽያንን አያያዝ በመቃወም የተቃውሞ ሰልፍ በተጠራ ማግስት መሆኑ ታውቋል፡፡

በሰሜን የአገሪቱ ክፍል ይንቀሳቀሳሉ የተባሉት ጽንፈኞቹ የእስላማዊ መንግሥት አማጽያን 49 የመንግሥት ወታደሮችን ከገደሉበት ጊዜ ጀምሮ በጦሩ አባላት ዘንድ በተፈጠረ ቅሬታ መፈንቅለ መንግሥት ሊካሄድ ይችላል የሚል ወሬ ሲነገር መቆየቱ ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG