በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሪታንያ በኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻ ዋዜማ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ብሪታንያ ነገ ማክሰኞ የኮቪድ-19 ክትባት ዘመቻዋን ስትጀምር የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ሰራተኞች፤ በአረጋውያን አረጋውያት መኖሪያዎች ሁሉ በወረርሽኙ በብርቱ የሚጎዱ ዜጎች እና እንክብካቤ የሚያደርጉላቸው ባለሞያዎች ግዙፉ የዩናይትድ ስቴትሱ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ፋይዘር የጀርመኑ የሕክምና ቴክኖሎጂ ኩባንያ ባዮ ኢንቴክ በጋራ የሰሩትን ክትባት መስጠት ትጀምራለች።

የሃገሪቱ የሕክምና ጉዳዮች ተቆጣጣሪ ድርጅት የክትባት መድሃኒቱ ጥቅም ላይ እንዲውል የአስቸኳይ ጊዜ ፍቃድ በሰጠ ልክ በሳምንቱ የሚጀመረው የክትባት ዘመቻ ብሪታንያን ክትባቱ ለሕዝብ እንዲሰጥ በመፍቀድ የመጀመሪያዋ ምዕራባዊት አገር ያደጋታል።

እንግሊዝ የተባለውን የአስቸኳይ ጊዜ ፍቃድ ያጸደቀችው ፋይዘር በሰዎች ላይ የሚደረገው የመጨረሻው መጠነ ሠፊ ሙከራ ክትባቱ መስራቱን የሚያሳይ እጅግ ከፍተኛ የስኬት ውጤት ማስመዝገቡን ይፋ ባደረገ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ነው።

ብሪታንያ ከገዛችው ፋይዘር/ባዮ ኢንቴክ ሰር 40 ሚልዮን ክትባት 800 ሺውን በትላንትናው ዕለት መረከቧ ተገልጧል።

የፋይዘር ክትባት ከ90 በመቶ በላይ ውጤታማ መሆኑ ታወቋል። ይህም ውጤት በክትባት መድሃኒቶች ፍቱንነት እጅግ ከፍተኛ ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ነው። በአንጽሩ የፋይዘርን ክትባት ፈጣን ሥርጭት አዳጋችና ውስብስብ ከሚያደርጉት ነገሮች ውስጥ ከዜሮ በታች 70 ዲግሪ ሴንቲግሬድ የቅዝቃዜ መጠን ማቆየት ከሚችል ማቀዝቀዣ ውስጥ መቀመጥ ማስፈለጉ ይገኝበታል።

ክትባቱ ብርቱ የጎንኞሽ ውጤት ያመጣ ይሆናል በሚል ያልተጨበጠ (በጥናቶቹ ያልታየ) ሥጋት ሳቢያ ከመከተብ ሊቆጠቡ የሚችሉ ሰዎችን ያለ ስጋት ክትባቱን እንዲወስዱ ለማበረታታት የ94 ዓመቷ ንግስት ኤልሳቤጥ 2ተኛ እና የ99 ዓመት ዕድሜ ባለ ጸጋው ባለቤታቸው ልዑል ፍሊፕ የሚከተቡ መሆናቸውን ዛሬ ይፋ ያደርጋሉ ተብሏል።

XS
SM
MD
LG