በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ስለአፍጋኒስታ ቀውስ ንግግር ሊደርጉ ነው


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ስለአፍጋኒስታን ቀውስ ለአሜሪካ ህዝብ ንግግር ያደርጋሉ።

ፕሬዚደንቱ ታሊባን አፍጋኒስታንን ሙሉ በሙሉ ከተቆጠጣረ ወዲህ ይህ የመጀመሪያ ንግግራቸው ይሆናል።

የታሊባን ተዋጊዎች ትናንት ዋና ከተማዋ ካቡል ከገቡ በኋላ ፕሬዚዳንቱ አሽራፍ ጋኒ ከሀገሪቱ ወጥተዋል።

በዜናው መሰረት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባይደን ከካምፕ ዴቪድ ወደዋይት ሃውስ ይመለሱ እና በዋሽንግተን ሰዓት ከአንድ ሰዐት ከአርባ አምስት ደቂቃ በኋላ ማለትም ዘጠኝ ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ ላይ ንግግር ያደርጋሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ታሊባን የሰው ህይወት እንዳይጠፋ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳሰበ።

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ እንቶንዮ ጉቴሬዥ ዓለም ይህን አፍጋኒስታን ያለችበትን አሳሳቢ እና ወሳኝ ሁኔታ እየተከታተለ ነው ብለው የታሊባን ሃይሎች የሀገሪቱን ህዝብ ደኅንነት ለመጠበቅ እና ችግር ላይ ላሉት ሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ዛሬ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸኃፊ ለጸጥታው ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ባደረጉት ንግግር "የአፍጋኒስታንን ህዝብ ፊታችንን ልናዞርበት ልንተወው አንችልም አይገባንምም" ብለዋል። ግጭቱ ባስቸኳይ እንዲቆም እና የሀገሪቱ ህዝብ በሙሉ መብቶቹ እንዲከበሩ እጠይቃለሁ ያሉት ጉቲሬዥ የሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ በተለይ የአፍጋን ሴቶች እና ልጃገረዶች ጉዳይ እጅግ የሚያሳስባቸው መሆኑን ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG