በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ስለመምረጥ መብት ውሳኔዎች ለመቀስቀስ ወደ ጆርጂያ ሄዱ


ፎቶ ፋይል፦ በአትላንታ ጆርጂያ መራጮች ድምፅ ለመስጠት ሰልፍ ቆመው፣ እአአ ዴሴምበር 14/2020
ፎቶ ፋይል፦ በአትላንታ ጆርጂያ መራጮች ድምፅ ለመስጠት ሰልፍ ቆመው፣ እአአ ዴሴምበር 14/2020

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ የመምረጥ መብትን ያረጋግጣል የተባለውን ረቂቅ ህግ ለማስተዋወቅና ድጋፍ ለማሰባሰብ ዛሬ ወደ ደቡባዪቷ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ጆርጂያ ማቅናታቸው ተገለጠ፡፡

የዋይት ኃውስ ባለሥልጣናት ባይደን በዚህ ጉዟቸው የመምረጥ መብት ነጻና ከወገንተኝነትና ማጭበርበር በጸዳ መልኩ አስተማማኝነቱ በተጠበቀ መልኩ ስለሚካሄድበት መንገድ ይሟገታሉ ብሏል፡፡

እነዚህ መብቶች ማረጋገጥ የሚቻለው የመምረጥ መብትን የሚያረጋግጡ ሁለቱ የህግ ረቂቆች መሆናቸውን ተፈጻሚ ሲሆኑ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ባይደን ባወጡት ዛሬ ባወጡት የትዊት መልዕክታቸው “ታሪክ የመራጮችንድምጽ ለሚያፍኑት ሁሉጥሩ ሆኖ አያውቅም የመመረጥ መብትን ለማያስከብሩትም መልካም አይሆንም” ብለዋል፡፡

ሁለቱን የምርጫ መብት የሚያረጋግጡ የህግ ረቂቆች በመወሰኛው ምክር ቤት ለማሳለፍ እንዲረዳ የምክር ቤቱን አሰራር የሚየቀረውን ህግ እንዲጸደቅ ባይደን ጥረት ያደርጋሉ ሲልም ዋይት ኃውስ በመግለጫው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG