በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የዩክሬኑን ልምድ በእስያ ፓስፊክ ተጽእኖ ላሳደረችው ቻይና መልዕክት ማስተላለፊያ አድርገውታል


ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በቶኪዮ ጉባኤ ጃፓን
ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በቶኪዮ ጉባኤ ጃፓን

በእስያ ያደረጉትን የ6ቀናት ጉዞ በማጠናቀቅ ላይ የሚገኙት ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የዩክሬኑን ጦርነት ቻይና ዓለም አቀፉን ሥርዓት እንድትጠብቅ መልዕክት ማስተላለፊያ አድርገው የተጠቀሙበት መሆኑ ተገለጸ፡፡

ባይደን በቶኪዮ ጉባኤ ከጃፓን፣ ህንድና አውስትራሊያ፣ በቡድን አጠራራቸው ኳድ አራት ተብለው ከሚጠሩት አገራት መሪዎች ጋር ባደረጉት ስብሰባ፣ ባሰሙት ንግግር “የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት፣ ዓለም አቀፍ ህግና የሰብአዊ መብቶች በየትኛውም የዓለም ክፍል ቢሆን፣ ሁልጊዜም የተጠበቁ ናቸው” ብለዋል፡፡

የሩሲያው የዩክሬን ወረራ “ነጻ፣ ክፍትና፣ እርስ በርሱ የተገናኘ፣ ደህንነቱ የተረጋገጠ፣ ምንም ነገር መቋቋም የሚችል፣ የኢንዶ ፓስፊክን መፍጠር” የአስተዳደራቸው ዋነኛው ስትራቴጂክ ግብ መሆኑን ባይደን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

ምንም እንኳ የአራቱ አገሮች መሪዎች ንግግር ቻይናን በቀጥታ በስም የጠቀሰ ባይሆንም፣ ሉዐላዊነትንና የህግ የበላይነት የጠበቀ፣ የኢንዶ ፓስፊክ ቀጠናን መመስረት የሚሉት የዲፕሎማሲ ቃላት ወደ ቻይና የሚያመላክቱ መሆኑን ተነግሯል፡፡

ቤጂንግ በቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ የባህር ኃይሏን ጨምሮ በሚያስደንቅ መልኩ ወታደራዊ ወጭዎችዋንና በጀቶችን የጨመረች መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከዩናትድ ስቴትስ ቀጥሎ ቻይና ትልቅ የመከላከያ በጀት ያላት አገር እንደሆነች ተገልጿል፡፡

ብዙዎቹ ቻያና ታዋይንን ልትወር ትችላለች የሚል ሥጋት ቢኖራቸውም የቻይና ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚታየው ቻይና ቢያንስ ሶስት ሰው ሰራሽ ወደቦችን ወደ ወታደራዊ የጦር ሰፈር በቀየረችባቸው አወዛጋቢው የደቡብ ቻይና ባህር አካባቢዎች መሆኑን ተመልክቷል፡፡

የቻይናው ፕሬዚዳንት ይህን እንደማያደርጉ ቀደም ሲል ለዓለም የማስተማመኛ ቃል ሰጥተውበት እንደነበር ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG