በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤት የመሳሪያ ቁጥጥር እርምጃዎችን እንዲፈቅድ ባይደን አጥብቀው ተማጸኑ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሜሪካውያንን በከፍተኛ ደረጃ እያስፈሩ ያሉትን ደም አፋሳሽ የጅምላ ተኩስ ጥቃቶች ለማስቆም “ትክክለኛ እርምጃዎች” ሲሉ የጠሯቸውን እርምጃዎች የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት እንዲፈቅድ አጥብቀው ተማጸኑ፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ትናንት ሀሙስ ማታ በዋይት ኃውስ ባደረጉት ንግግር በመሳሪያ የሚፈጸም ጥቃትን ለመዋጋት የሚረዱ ያሏቸውን አዳዲስ የቁጥጥር እርምጃዎችም አቅርበዋል፡፡

ምክር ቤቱ እአአ በ1994 የወጣውን እና በ2004 ያበቃውን የከፊል ኦቶማቲክ እና በእሩምታ ተኳሽ እና ብዙ ጥይት ጎራሽ ጠብመንጃዎች እገዳውን መልሶ ሥራ ላይ እንዲያውል ፕሬዚዳንቱ ተማጽነዋል፡፡

መሳሪያ የሚገዙ ሰዎች የኋላ ታሪክ ፍተሻ እንዲጠናከር ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ ተብለው ከሚታሰቡ ወይም የአእምሮ አለመረጋጋት ከሚያሳዩ ግለሰቦች ላይ ለተወሰነ ጊዜ መሳሪያቸውን መውረስ የሚያስችል እና መሳሪያን በተገቢው መንገድ ማስቀመጥን ጨምሮ ሌሎች ህግጋት እንዲወጡ ፕሬዚዳንቱ ጠይቀዋል፡፡

የጦር መሳሪያ አምራች ኩባኒያዎችን ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገው ህግ እንዲሰረዝም ፕሬዚዳንቱ ተማጽነዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ያቀረቧቸው ሃሳቦች በፖለቲካ አቋም በተከፋፈለው እና አባላቱም የመሳሪያ ቁጥጥር ህግን በሚመለከት በማይስማሙበት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት የሚጸድቁላቸው አይመስልም፡፡

XS
SM
MD
LG