በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ከአቡነ ፍራንሲስ ጋር በቫቲካን ተወያዩ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ዛሬ ዓርብ በቫቲካን ተገናኙ
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ዛሬ ዓርብ በቫቲካን ተገናኙ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ዛሬ ዓርብ በቫቲካን ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

ባይደን እንደ ግልና የፖለቲካ ግንኙነት ተደርጎ በታየው በዚሁ ፕሮግራም ላይ የተገኙት፣ ከዚህ በኋላ በሚደረገው የቡድን 20 አባል አገራት መሪዎች ጉባኤ ላይ ፣ ስለ ዓለም ምጣኔ ሀብት፣ ከዚያም በስኮትላንድ ግላስኮ ላይ በሚደረገው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ከመሳተፋቸው በፊት ነው፡፡

ባይደን ከሊቃነ ጳጳሳቱ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ እስካዛሬ በካቶሊክ አማኝነታቸውና በምድራዊ የፖለቲካ ሰውነታቸው የሚመሩትን ዓላማዊ መንግሥት ለማስታረቅ በሚታገሉባቸው፣ እንደ ጾታዊ ግንኙነትና ስነ ውልደትና ውርጃ፣ በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ መነጋገር እንደሚጠበቅባቸው ተገምቷል፡፡

ሊቃነ ጳጳሳቱ ፍራንሲስ፣የባይደን ቤተሰብ ሀዘን በገጠመው ጊዜ በቅርብ ተገኝተው ሲያጽናኗቸው የነበረ መሆኑን ይታወቃል፡፡

ሁለቱም መሪዎች ቢያንስ ሶስት ጊዜ በአካል የተገናኙ ሲሆን የደብዳቤ ልውውጦችንም አድርገዋል፡፡

ዋይት ሀውስ፣ የባይደን የቫቲካን ጉብኝትና ከሊቃለ ጳጳሳቱ ጋር መገናኘት ሙሉ ለሙሉ እንደ ግል ጉዳይ ተደርጎ መወሰድ እንደሚገባው አጽንኦት በመስጠት አሳስቧል፡፡

የዋይት ሀውስ የደህንነት አማካሪ ጄክ ሱሊቫን፣ ትናንት ሀሙስ በሰጡት መግለጫ፣ ምንም እንኳ ግንኙነት በግል ቢሆንም፣ ሚሊዮን ተከታዮች ያላቸው ሁለቱ ታላቅ መሪዎች፣ “ዓለም አቀፋዊ በሆኑ ትላልቅ ፖሊሲዎች ላይ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል” ብለዋል፡፡

ከፕሬዚዳንት ባይደን ጋር አብረው የተጓዙት፣ ባለቤታቸው ጂል ባይደን፣ በሰዎች ክብር፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዙሪያና ድሆችን በመንከባከብ በኩል አብሮ መስራት ስለ ሚቻልበት ሁኔታ እንደሚወያዩ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG