በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን የማህበራዊ ደህንነት ዋስትና እቅዳቸውን በግማሽ ቀነሱ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ለአሜሪካውያን ቤተሰብ፣ እስከ ዛሬ በአስርት ዓመታት ውስጥ፣ በዘለቄታዊነቱ ወደ የሌለው ድጋፍ ይሰጣል ያሉትን፣ የ1.85 ትሪሊዮን ዶላር፣ የበጀት እቅድ በትናንትናው እለት ይፋ አድርገዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የአረንጓዴ ጋዝ ብክለትን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ የሚያስችለውን አቅጣጫ መያዟ ተመልክቷል፡፡ ባይደን ከትናንት በስቲያ ጠዋት፣ ከዴሞክራት የምክር ቤት አባላት ጋር ከተነጋገሩ በኋላ፣ ከሳምንታት በፊት ካስተወዋቁት የበጀት እቅዳቸው በግማሽ ቀንሰዋል፡፡ እዚህ የደረሱት የተለያየ አቋም የያዙትን የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባላትን ጨምሮ የ3.5 ትሪሊዮን ዶላር እቅዳቸውን ከተቃወሙት ጋር ሁሉ ብርቱ የፖለቲካ ትግል በማድረግ መሆኑን ባይደን ገልጸዋል፡፡ “ማንም ሰው የፈለገውን አያገኝም፣ እኔም ጨምሮ” በማለት መስማማት አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱን ያቀረቡትን የወጭ እቅድ “በአገራችንና ህዝባችን ላይ የምናውለው ታሪካዊ ኢንቨስትመንት ነው” ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ይህኛው እቅድ የሁለቱንም ምክር ቤቶች ድጋፍ አግኘቶ እንደሚጸድቅም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡

XS
SM
MD
LG