በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዴሞክራቶቹ በፕሬዚዳንቱ የ3.5 ትሪሊዮን ዶላር እቅድ እየተነጋገሩ ነው


የህግ መወሰኛው ምክር ቤት
የህግ መወሰኛው ምክር ቤት

ዴሞክራቶቹ የዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባላት በትልቁ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የማህበራዊ ደህንነትና ዋስትናና የአየር ንብረት ለውጥ የበጀት እቅድ ድርድር ላይ አሁንም እንደተጠመዱ ናቸው፡፡

በተለይ በበጀት እቅዱ ውስጥ የትኞቹ መያዝ፣ የትኞቹ መወገድ አለባቸው? ወጭዎቹስ የሚሸፈኑት እንዴትና በማን ነው? የሚሉት ዋነኛ መነጋገሪያ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ትናንት ምሽት፣ ለሚቀጥሉት 50 ዓመታት፣ የአሜሪካውያን ቤተሰቦችን ጥቅማ ጥቅም ያስጠብቃል የተባለውን፣ የ3.5 ትሪሊዮን ዶላር የበጀት እቅዳቸውን ከሚቃወሙት፣ ከዌስት ቨርጂኒያው ሴነተር ጆ ማንሺን፣ እና ከአሪዞናው ሴነተር ኪርስተን ስነማ ጋር ትናንት ምሽት በዋይት ሀውስ ተገናኝተው መክረዋል፡፡

መሳ ለመሳ በሆነው የህግ መወሰኛው ምክር ቤት የሁለቱ ሴነተሮች ድምጽ የፕሬዚዳንቱን እቅድ ለማጸደቅ ወሳኝ መሆኑ ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG