በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንክን በሩሲያና ዩክሬይን ጉዳይ ለመምከር ወደ ዩክሬን እና ጀርመን ሄዱ


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ሩሲያ በዩክሬን ወረራ ልትፈጽም እየተዘጋጀች ነው የሚል ሥጋት ባለበት ወቅት ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ጋር ለመነጋገር ወደ ዩክሬን መሄዳቸው ተነገረ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዛሬ ማክሰኞ በአጣዳፊ የተዘጋጀው ጉዞ ብሊንከን ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚየር ዘለንስኪ እና የውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ ዲምትሮ ኩሊባ ጋር ነገ ረቡዕ ኪየቭ ውስጥ ተገናኘተው እንዲነጋገሩ በመታቀዱ እንደሆነ አስታውቋል፡፡

የሚኒስቴሩ መግለጫ ጨምሮ እንዳመልከተው የጎዞው ዓላማ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት መጠበቅ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብሏል፡፡

ብሊንከን ወደ ጀመርን በማቅናት ከጀመርን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አናሌና ባሬቦክ ጋር እንደሚገናኙና በሩሲያው ጉዳይ ስላለው የዲፕሎማሲ ጥረት እንደሚነጋገሩም መግለጫው አመልክቷል፡፡

በሌላ ዘገባም የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩሲያን እንደሚጎበኙ ተነግሯል፡፡

የብሊንከን ጉዞ ባላፈው ሳምንት ውስጥ በሩሲያና ዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት መካከል ዩክሬን አስመልክቶ በጄኔቭ የተካሄደው ስብሰባ ያለምንም ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG