በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት በአሜሪካ


የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ በኔት
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ በኔት

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ በኔት ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር በዛሬ እለት በዋይት ሐውስ ተገናኝተው በኢራን፣ በደህንነትና በኮቪድ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢራን የኒዩኪለር ቦምብ ባለቤት ልትሆን ትችላለች የሚል ስጋት እንዳለቸውም ተናግረዋል፡፡

ሁለቱም መሪዎች ከተመረጡ በኋላ ሲገናኙ ይህ የመጀመሪያቸው ጊዜ ነው፡፡ የ እስራኤሉ መሪ ከባይደን በተጨማሪ ከአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን ጋር ተገናኝተዋል፡፡

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት ቤኔት ሲናገሩ ፣ የአሜሪካ ህዝብ እስራኤል ስለ ኢራን ያላትን አስተሳሰብ እንዲገንዘብ እንደሚያደርጉ ተስፋቸውን ተናግረዋል፡፡

“ከእስራኤል አዲስ መንፈስ ይዤ ነው የመጣሁት፡፡ አንዳንድ ጊዜ ልዩነት ቢኖራቸውም በጥሩ መንፈስና ትብብር አብረው የሚሰሩ ወዳጆችን መንፈስ” ብለዋል፡፡

አሜሪካና ኢራን የተፈራረሙትን የኒዩኩሊየር ስምምነት ፕሬዛዳንት ትራምፕ በ2018 ሲመጡ የሰረዙት መሆኑን ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG