በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤንሻንጉል ጉምዝ የዛሬ ሁኔታ ላይ ጄነራል አሥራት ዴኔሮ ይናገራሉ


ሌ.ጄኔራል አስራት ዴኔሮ
ሌ.ጄኔራል አስራት ዴኔሮ

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ተፈናቅለው የነበሩ ከ50 ሺሕ በላይ ዜጎችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ እየተካሄደ መሆኑን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ ገለፁ።

በዞኑ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አሉ በማለት ጫካ ገብተው በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ የነበሩ ያሏቸውን ታጣቂዎችን የተሃድሶ ስልጠና ተሰጥቷቸው ወደ አካባቢው እንዲመለሱ ተደርጏል፤ በዚህም አካባቢው ሰላም ሆኗል ነው ያሉት ሌ/ጀኔራል አስራት።

ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ቆይታ ያደረጉት የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጄነራል አስራት ዴኔሮ ከመተከል ዞኑ ተፈናቅለው የነበሩ ከ50 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ወደ ቀድሞ ቀያቸው መመለስ የቻሉት ከተፈናቃዮቹ ጋር በነበረ ውይይት የሁለቱ ክልል አመራሮችና የፌዴራል መንግሥቱ ባደረጉት ስምምነት ታጣቂዎቹ የሰላም አማራጩን ተቀብለው በመግባታቸው እንዲሁም የፀጥታ ኃይሉ በከፈለው መስዋዕትነት ነው ብለዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በቤንሻንጉል ጉምዝ የዛሬ ሁኔታ ላይ ጄነራል አሥራት ዴኔሮ ይናገራሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00


XS
SM
MD
LG