በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአውሮፓ ተቃዋሚዎች በሩሲያ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ የኔቶ ዋና መሥሪያ ቤት ብራስልስ
ፎቶ ፋይል፦ የኔቶ ዋና መሥሪያ ቤት ብራስልስ

በዚህ ሳምንት ብራስል በሚደረገውን የኔቶ ስብሰባ ተስታፊ የሆኑ የአውሮፓ መሪዎች ተጨማሪና ጠናክራ ማዕቀብ እንዲወስዱ ግፊት ለማድረግ፣ በዩክሬን የሚካሄደው የሩሲያ ወረራ የሚቃወሙ ሰዎች በብራስልስ ተሰብሰበዋል፡፡

መሪዎቹ በሚሰበሰቡትና ከፕሬዚዳንት ባይደን ጋር በሚገናኙበት በአውሮፓ ኮሚሽን ዋና ጽ/ቤትና በአውሮፓ ምክር ቤት ህንጻ ፊት ለፊት የተሰባሰቡት ተቃዋሚዎቹ ትናትን ማክሰኞ ለዩክሬን ሰላም በመመኘት ትልቅ ሻማ አብርተዋል፡፡

ከሰልፉ አስተባባሪ አንዱ የሆኑት ፓስካል አቫዝ እንዲህ ብለዋል፣

“ዛሬ ምሽት የአውሮፓ እምብርት በሆነቸው በዚህች ስፍራ የተገኘነው ለአውሮፓ መሪዎች ግልጽ መልዕክት ለማስተላለፍ ነው፡፡ የፑቲንን ነዳጅ መጠቀም አቁሙ፡፡

በየቀኑ ወደ 250 ሚሊዮን ዩሮ በቀጥታ ፑቲን ለጦርነት እንዲጠቀምበት እንልካለን፡፡ በማሪፑል እና በየቦታው ያለ የዩክሬን ህዝብ በከፍተኛ ስቃይ ውስጥ ነው፡፡ ጊዜው እያመለጠን ነው፡፡ የአውሮፓ መሪዎች በዚህ ሳምንት አሁኑን እምርጃ እንዲወድሱ እንፈልጋለን፡፡”

አዋዝ ወደሩሲያ የሚጎርፈው ገንዘብ መቆም አለበት የሚጣለው ማዕቀብም ሊጨምር ይገባል ብለዋል፡፡ ተቃዋሚዎቹ በነገው እለት በብራስልስ ከሚሰበሰቡት መሪዎች ጋር ፊት ለፊት ስለመገናኘታቸው የተገለጸ ነገር የለም፡፡

XS
SM
MD
LG