በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦስትሪያ ምድር ባቡር ሠራተኞች የሥራ ማቆም አድማ አደረጉ


የኦስትሪያ የባቡር ጣቢያ
የኦስትሪያ የባቡር ጣቢያ

በኦስትሪያ የምድር ባቡር ሠራተኞች አንድ ሚሊዮን መንገደኞችን ጉዞ ማስተጓጎሉ የተነገረለትን የአንድ ቀን የሥራ ማቆም አድማ ዛሬ ሰኞ አድርገዋል፡፡

በክፍያ ውዝግብ ምክንያት በተጠራው የሥራ ማቆም አድማ ሁሉም የባቡር ትራፊክ አገልግሎት እንደሚቋረጥ የሠራተኞቹ ማህበር አስጠንቅቋል፡፡

አድማው በእቃ ማጓጓዣዎች፣ በክልልና የረጅም ርቀት ጉዞዎችን እንዲሁም በሌሊት መስመሮችም ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡

ጥያቄው ካልተመለሰ አድማው እንደሚቀጥል ያስጠነቀቀው ማኅበሩ አድማውን የጠራው ለአምስተኛ ጊዜ የተደረጉት ድርድሮች ባለመሳካታቸው መሆኑን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG