በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦስትሪያ ምርጫ ነባሩ ፕሬዚዳንት በድጋሚ ተመረጡ


ፎቶ ፋይል፦ የኦስትሪያ ፕሬዚዳንት አሌግሳንደር ቫን ደር ቤለን
ፎቶ ፋይል፦ የኦስትሪያ ፕሬዚዳንት አሌግሳንደር ቫን ደር ቤለን

የኦስትሪያው ፕሬዚዳንት አሌግሳንደር ቫን ደር ቤለን ሌላ የስድስት ዓመት ሁለተኛ የሥልጣን ዘመን እንደሚኖራቸው በሚያስተንማምን የድምፅ ብልጫ አረጋግጠዋል።

ትናንት እሁድ የተደረገው ምርጫ የቅድሚያ ውጤቶች እንደሚያሳዩት፣ 95 በመቶ ድምፅ የተቆጠረ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 56.1 በመቶውን ቫን ደር ቤለን ሲያገኙ፣ የቅርብ ተቀናቃኛቸውና የቀኝ ዘመሙ ወግ አጥባቂ “ነፃነት ፓርቲ” ወኪል ዋልተር ሮዘንክራዝ 17.9 ድምፅ አግኝተዋል።

አሌግሳንደር ቫን ደር ቤለን ማሸናፋቸውን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር በምርጫ ያገኙት ድል ለአውሮፓ ድል ነው ብለዋል።

“የአውሮፓን አንድነትን እና የሩሲያ ወራሪነትን በተመለከተ ያለን ግልፅ አቋም አሸንፏል። የተወዳዳሪዎቻችን አቋም ግልፅ አልነበረም” ብለዋል።

የ78 ዓመቱ ፖለቲከኛ ከዚህ በፊት ሃገሪቱ ቀውስ ውስጥ በገባች ግዜ በማረጋጋት ረገድ በነበራቸው ሚና ተወዳጅነትን አትርፈዋል። ከሚጠቀሱትም እአአ በ2019 መንግሥት ሲበተንና፣ በእአአ በ2021 ደግሞ ቻንስለር ሰባስቴይን ኩርዝ በሙስና ውንጀላ ምክንያት ስልጣን በለቀቁ ወቅት በነበረው ብሄራዊ ቀውስ ወቅት የተጫወቱት ሚና ይገኙበታል።

በኦስትሪያ ፕሬዚዳንቱ በአብዛኛው ሥነ ሥርዓታዊ ሥልጣን ቢሆንም፣ በቀውስ እና በሽግግር ወቅት ሃገሪቱን የመምራት ከፍተኛ ሥልጣን አለው።

በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሲሆን፣ መንግሥትን በጠቅላላ ወይም ቻንስለሩን የማስወገድ ሥልጣንም አለው።

XS
SM
MD
LG