በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውስትራሊያ በአንታርቲካ አህጉር ለማጠናከር ያሰበችውን አሰሳ ቻይና ተቃወመች


ፎቶ ፋይል - በአንታርቲካ የበጋ ወቅት ፔንግዊን
ፎቶ ፋይል - በአንታርቲካ የበጋ ወቅት ፔንግዊን

አውስትራሊያ ለሳይንሳዊ አሰሳ እና ስትራቴጂ ዓላማዎች በአንታርቲካ ላይ የምታደርጋቸውን ቅኝቶች ለማስፋፋት ማቀዷን ቻይና ተቃወመች።

የአውስትራሊያ መንግሥት በርከት ያሉ የቅኝት ድሮኖችን፣ እና ረዥም ርቀት መብረር የሚችሉ ሂሊኮፕተሮችን በበረዷማው አህጉር ላይ የማብረር ዕቅዱን ይፋ አድርጓል። 570 ሚሊየን ዶላር የተመደበለት የአውስትራሊያ ዕቅድ ሥነ ምህዳራዊ እና ሰትራቴጂካዊ ዓላማ እንዳለው ተነግሯል።

የበረዶ ጅረት፣ የውሃ ምርምር እና እየጨመረ ያለውን የባህር ጠለል በተመለከተ የዘረጉ ጥናቶችን ለማጠናከር፣ ባልተዳሰሱ የአህጉሩ ሥፍራዎች ላይ ቅኝቱ እንደሚደረግ ተነግሯል።

የይገባኛል ጥያቄ ባለበት ቀጠና ቻይና የምታደረግው መስፋፋት አውስትራሊያን እንዳሳሰባት ሲነገር ሰንብቷል።

በአንታርቲካ ሥምምነት መሰረት ሥፍራው ከጦር ስምሪት እና ኒዩእሌር መሳሪያዎች ነፃ እንዲሆን መወሰኑን የሚያስታውሱት የአውስትራሊያው ብሄራዊ ዩኒቨርሰቲ የህግ ምሁር ዶናልድ ሮዝዌል፣ አንዳንድ ሀገራት ግን አህጉሩን ለጦር ዓላማ ፍላገት እንዳላቸው ጠቁመዋል።

የቻይና መንግሥት ልሳን የሆነው ግሎባል ታይምስ፣ ሀገሪቱ ሳይንሳዊ አሰሳዎችን በማድረግ ረገድ ሁልጊም የአንታርቲክ ሥምምነትን አክባሪ እንደሆነች አስታውሶ፣ የአውስትራሊያ የሚሊየን ዶላሮች ዕቅድ ግን የሀገሪቱ መንግሥት የያዘው ፀረ-ቻይና ዕቅድ አካል ነው ብሏል።

XS
SM
MD
LG