ዋሺንግተን ዲሲ —
አውስትራሊያ ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው ሁለት ክፍላተ ሀገሮች ካሁን ቀደም ባልታየ ደርጃ የበዙ የኮሮናቫይረስ ተያዦች መገኘታቸውን አስታወቀች።
ከፍተኛው የህዝብ ብዛት ባላት ኒው ሳውዝ ዌልስ በሃያ አራት ሰአት ጊዜ 680 ተጋላጮች ተገኝተዋል።
ቪክቶሪያ ክፍለ ሀገርም ሞልበርን ከተማ ውስጥ ሃምሳ ሰባት አዲስ የቫይረሱ ተያዦች እንደተመዘገቡ አስታውቃለች።
አውስትራሊያ ዴልታ የተባለውን የኮሮናቫይረስ ዝርያ መዛመት እየተዋጋች ባለችበት በዚህ ወቅት በሜልበርን ከተማ ለስድስተኛ ጊዜ የእንቅስቃሴ ዕገዳ ታውጇል።
ረቡዕ ዕለት አውስትራሊያ ውስጥ 747 አዲስ የቫይረሱ ተያዦች ተመዝግቧል። ቁጥሩ እስካሁን በአንድ ቀን ከተገኙት ሁሉ ትልቁ እንደሆነ ተገልጿል። በሀገሪቱ እስካሁን የኮቭድ ክታባት የተከተበው ከህዝቡ 22 ከመቶው ብቻ መሆኑን የጆንስ ሃፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ ማዕከል አሃዝ ያሳያል።