በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አውስትራሊያ ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦች ደነገገች


አውስትራሊያ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጧላን የሚሳይ በአውስትራሊያ እና በሩሲያ ባንዲራ ላይ።
አውስትራሊያ ሩሲያ ላይ ማዕቀብ መጧላን የሚሳይ በአውስትራሊያ እና በሩሲያ ባንዲራ ላይ።

አውስትራሊያ ሩሲያ ላይ በዩክሬይን ላይ ባደረሰችው ወረራ የተነሳ ተጨማሪ ማዕቀቦች ደንግጋባታለች። ከሩሲያ የሚወጡ እና እንቅስቃሴ ያቆሙ ምዕራባውያን ኩባንያዎች ቁጥር ጨምሯል።

አዲሶቹ ማዕቀቦች በሩሲያ የጦር ኃይልና የጦር አዛዦች ላይ ያነጣጠሩ መሆናቸውን የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ምሪስ ፒይን ተናግረዋል። በተጨማሪም የሩስያውን ወረራ ምክንያታዊ አድርጎ ለማቅረብ ክሬምሊን የወሰደውን እርምጃ ደጋፍ ፕሮፓጋንዳ የሚያሰራጩ ስማቸው በውል ያልተገለጸ አስር ግለሰቦችም በማዕቀቡ ዒላማዎች ዝርዝር ውስጥ እንደሚገኙበት ሚኒስትር ፔይን ገልጸዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ ሩሲያ ዩክሬይንን በመውረሯ የተነሳ በዚያች ሀገር የንግድ እንቅስቃሴያቸውን ያቋረጡ ወይም ሙሉ በሙሉ ለቀው የወጡ የምዕራባውያን የንግድ ተቋማት ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። ከበድ ባለ ሁናቴ የሩሲያን ኢኮኖሚ የሚጎዳው በነዳጅና ጋዝ ኢንዱስትሪው የተወሰደው እርምጃ መሆኑ ተጠቁሟል። መሰረቱ ብሪታንያ የሆነው ቢፒ የሩስያ መንግሥት ንብረት በሆነው ሮዝኔፍት የነዳጅና ጋዝ ኩባኒያ ውስጥ ያፈሰሰውን የአስራ አራት ቢሊዮን ዶላር መዋዕለ ነዋይ ማውጣቱን ባለፈው ዕሁድ አስታውቋል።

የብሪታንያው ሼል ኩባኒያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ቤን ቫን ቢዩርዲን ኩባኒያቸው ባለፈው ሳምንት ከሩሲያ ላይ ድፍድፍ ነዳጅ በመግዛቱ በዛሬው ዕለት ይቅርታ መጠየቃቸው ተዘግቧል። ሼል ሩሲያ ውስጥ የሚያካሂደውን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ እንደሚያቆምም አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG