በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአዲስ ጥቃት ሳቢያ ቆቦ ላይ ተፈናቃይ ሰፍሯል


ቆቦ ከተማ
ቆቦ ከተማ

በህወሓት አዲስ ጥቃት ምክንያት ከዋጃና ከአላማጣ አካባቢዎች ተፈናቅለው ሰሜን ወሎዋ ቆቦ ከተማ የተጠለሉ የከበደ የምግብና የአልባሳት እጥረት እንዳለባቸው አስታውቀዋል።

በጥቃቱ ሳቢያ ከ12 ሺህ በላይ ተፈናቃይ ቆቦ መስፈሩን የዋጃ ጥሙጋ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ ገልፀዋል።

ህወሓት ከትናንት ወዲያ አወጣው በተባለ መግለጫ “በአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ልዩ ፖሊስና በኤርትራ መንግሥት ይደገፋል” ባለው “የቀይ ባህር አፋር ኃይል” ሲል በጠራው ኃይል ላይ ጥቃት መክፈቱን አሳውቋል።

ታጣቂዎቹ በዋጃ፣ በጥሙጋና በአላማጣ አካባቢዎች አደረሱት በተባለው ጥቃት ዙሪያ ግን ህወሓት እስካሁን በይፋ ያለው ነገር የለም።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአዲስ ጥቃት ሳቢያ ቆቦ ላይ ተፈናቃይ ሰፍሯል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:57 0:00


XS
SM
MD
LG