በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጦርነት የተጎዳውን የዐማራ ክልል መልሶ ለመገንባት ከግማሽ ትሪሊዮን በላይ ብር ያስፈልጋል ተባለ

በጦርነት የተጎዳውን የዐማራ ክልል መልሶ ለመገንባት ከግማሽ ትሪሊዮን በላይ ብር ያስፈልጋል ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:02 0:00

በጦርነት የተጎዳውን የዐማራ ክልል መልሶ ለመገንባት ከግማሽ ትሪሊዮን በላይ ብር ያስፈልጋል ተባለ

በዐማራ ክልል፣ በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና በሌሎች ግጭቶች ሳቢያ የደረሰውን ውድመት ተከትሎ፣ 12 ሚልዮን የሚጠጋ ሕዝብ፥ በከፋ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ፣ በክልሉ፣ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋም እና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

የጽ/ቤቱ ዋና ዲሬክተር ዶር. አባተ ጌታሁን፣ ዛሬ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ ከሁለተኛው ዙር የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በኋላ የተደረገውን ጥናት መነሻ በማድረግ፣ በቅርቡ በተደረገው የክለሳ ጥናት፣ ክልሉ፥ በጦርነቱ እና ከጦርነቱ ጋራ በተያያዙ ግጭቶች የወደሙ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እና ለማቋቋም፣ 522 ቢልዮን ብር እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል፡፡

ለመልሶ ግንባታ የተጠየቀው ገንዘብ፣ እጅግ ከፍተኛ በመኾኑ፣ መንግሥታዊም ኾኑ መንግሥታዊ ያልኾኑ ድርጅቶች፣ የርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ፣ የጽ/ቤቱ ዋና ዲሬክተር ጥሪ አቅርበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG