በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰራቸውን ሰዎች እንዲፈታ በተለያዩ ወገኖች ተጠየቀ


የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰራቸውን ሰዎች እንዲፈታ በተለያዩ ወገኖች ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:01 0:00

የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰራቸውን ሰዎች እንዲፈታ በተለያዩ ወገኖች ተጠየቀ

የኢትዮጵያ መንግሥት “ሕግ የማስከበር ዘመቻ” በሚል እያካሄደ በሚገኘው የሰሞኑ እንቅስቃሴ አባሎቻቸዉ እና ደጋፊዎቻቸው ጭምር መታሠራቸውን የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) እና እናት ፓርቲ አስታወቁ።

በፖለቲካ አቋማቸው ምክንያት የታሠሩ ያላቸው ሰዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ አብን ጠይቋል።

በሌላም በኩል የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በቅርቡ የታሰሩ ጋዜጠኞችን እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችን በሙሉ መፍታት እንዳለባቸው ዓለም አቀፉ የጋዜጠኛች መብት ተሟጋች ድርጅት ሲፒጄ ትናንት ባወጣው መግለጫ አሳስቧል።

ዩናይትድ ስቴትስም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የሕግ የበላይነትን እንዲያከብሩ አሳስባለች።

ማምሻውን መግለጫ ያወጣው የአማራ ክልል መንግሥት ሕግና ሥርዓትን የማስከበር ግዴታውን እየተወጣ ያለው ሕግን በማክበር እንደሆነ በመግለፅ የሚቀርቡበትን ትችቶች ተከላክሏል።

XS
SM
MD
LG